News

ከመጋቢት 29-30/ 2015 ዓ.ም በውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ በጅማ ከተማ በቴማቲክ ፕላኖች ላይ በአባይ ቤዚን ውስጥ ከሚገኙ የኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የውይይቱን መርሀ ግብር በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የወንደወሰን መንግሥቱ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደገለጹት የአባይ ቤዚን ፕላን ሲዘጋጅ ለሀገራችን አዲስ ሀሳብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ጠቅሰው ችግሮቹን ለመፍታት አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመር የቤዚን ፕላን ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት መቻሉን ገልፀዋል። ቤዚን ፕላኑን ለማዘጋጀት፤ በተፋሰሱ ውስጥ ያሉ አቅሞች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ የሁኔታ ዳሰሳ ሥራዎችን መሰራታቸውን ገልጸው፤ የአከባቢ ሁኔታ፣ የውሃ ሀብት አቅም፣ የተቋማዊና ህጋዊ ሁኔታና የአደጋ ስጋት ትንተናዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። የቤዚን ብላኑን ለመተግበር የተዘጋጁ ቴማቲክ ዕቅዶች ማለትም ዌትላንድ ማኔጅመንት፣ የመሬት መንሸራተት፣የውሃ ጥራት፣የቤዚን ኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት፣የበለስና ዴዴሳ የውሃ ምደባ ዕቅዶች ቀርበው ውይይት ተደረጎባቸዋል፡፡

የመገጭ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና እንክብካቤ ፕሮጀክት

በአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የመገጭ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማትና እንክብካቤ ፕሮጀክት የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ታህሳስ 07/2015ዓ/ም በጎንደር ከተማ በተካሄደበት ወቅት!

Remote sensing and climate data model Application Training

የአባይ ቤዝን አስተዳደር ጽ/ቤት ከWRI ጋር በሀቅም ግንባታ እና የእውቀት ሽግግር ለመተግበር በትብብር ለመስራት በተደረሰው ስምምነት መሰረት ለተቋሙ ባለሙያዎችና ለአጋር አካላት በተዘጋጀው Remote sensing and climate data model Application የድርቅ ክስተትና ተጋላጭነት ለመተንበይ እንዲቻል የሚያግዝ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ከአባይ ቤዝን አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ከውሃና ኢነርጅ ቢሮ ፣ከዩኒቨርስቲዎች፣ከዲዛንና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ፣ከአዋሽና ከስምጥ ሸለቆ ኃይቆች ቤዝን አስተዳደር ጽ/ቤት ለተወጣጡ በአጠቃላይ 27 ባለሙያዎች ከ24-26/2015 ዓ.ም ለሶስት ቀናት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በባህርዳር ከተማ ተሰጥቷል፡፡ ይህንን ስልጠና ተግባራዊ ለማደረግ ስልጠኛ የተሳተፉ ባለሙያዎችን በአራት ግሩብ በመመደብ የዲንደር የበሽሎ የራይድን የወለቃ ን/ቤዝኖች Hydrologic Drought Analysis ለመሰራት ተግባር የተሰጠ ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ስራ ሲጠናቀቅ Validatuion ታይቶ ከፀደቀ በኃላ ወደ ትግበራ እንዲገባ ታቅዷል፡፡

ክፍተት መሙላት፣እውቀትና ልምድ ማጋራት፣በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች በመለየት በብቃት መፈፀምና ልምድና ተሞክሮ በመቀየር ወደ ሌሎች ን/ቤዝኖች እንዲሰፉ ማድረግ ከስልጠናው የሚጠበቅ መሆኑ ተገልጧል፡፡

Training group photo

You missed

ከመጋቢት 29-30/ 2015 ዓ.ም በውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ በጅማ ከተማ በቴማቲክ ፕላኖች ላይ በአባይ ቤዚን ውስጥ የሚገኙ የኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የውይይቱን መርሀ ግብር በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የወንደወሰን መንግሥቱ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደገለጹት የአባይ ቤዚን ፕላን ሲዘጋጅ ለሀገራችን አዲስ ሀሳብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ጠቅሰው ችግሮቹን ለመፍታት አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመር የቤዚን ፕላን ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት መቻሉን ገልፀዋል። ቤዚን ፕላኑን ለማዘጋጀት፤ በተፋሰሱ ውስጥ ያሉ አቅሞች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ የሁኔታ ዳሰሳ ሥራዎችን መሰራታቸውን ገልጸው፤ የአከባቢ ሁኔታ፣ የውሃ ሀብት አቅም፣ የተቋማዊና ህጋዊ ሁኔታና የአደጋ ስጋት ትንተናዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። የቤዚን ብላኑን ለመተግበር የተዘጋጁ ቴማቲክ ዕቅዶች ማለትም ዌትላንድ ማኔጅመንት፣ የመሬት መንሸራተት፣የውሃ ጥራት፣የቤዚን ኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት፣የበለስና ዴዴሳ የውሃ ምደባ ዕቅዶች ቀርበው ውይይት ተደረጎባቸዋል፡፡