ቀን 03/02/2015 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ.ቤ.አስ.ጽ/01.1/2015
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ እቃወችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታው ሰነድ የሎት (lot) መለያ
- ሎት – 1. የጋቢዮን ሳጥን እና የጋቢዮን ማሰሪያ ሽቦ
- ሎት – 2. የችግኝ መትከያ ፕላስቲክ ቲዩብ
- ሎት -3 የግብርና ዕቃዎች
- ሎት – 4. ዶዘር እና ኤክስካቫተር ማሽን ኪራይ
- ሎት – 5. GPS
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፋ የተሰማሩ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1.ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
2.ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. የሚገዙ እቃወች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 119 መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት
ሎት- 01 የጋቢዩን ሳጥንና ማሰሪያ ሽቦ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር /
ሎት- 02 የችግኝ መትከያ ፕላስቲክ ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር)
ሎት- 03 የግብርና ዕቃዎች ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሽህ ብር)
ሎት- 04 የማሽን ኪራይ (ዶዘርና እስካቫተር) ብር 40,000(አርባ ሽህ ብር)
ሎት 05 GPS ብር 10,000/ አስር ሽህ ብር / በአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ስም በባንክ
በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማሰያዝ አለባቸው፡፡
6.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ እና በድርጅቱ ማህተም በተደረገበት ፖስታ እያንዳንዱ ሎት ፖስታዉ ላይ ተጽፎ ባህር ዳር በሚገኘው ብልጽግና ጽ/ቤት ጎን የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 15 ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማሰገባት ይጠበቅበዎታል፡፡
7.የጨረታ ሳጥኑ በአስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ተወካዩች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የሚከለክል አይሆንም፡፡
8.የጨረታው መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፣
9.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
10.ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ወይም ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583213144 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡