Assosa Branch Office

You missed

ከመጋቢት 29-30/ 2015 ዓ.ም በውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ በጅማ ከተማ በቴማቲክ ፕላኖች ላይ በአባይ ቤዚን ውስጥ የሚገኙ የኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የውይይቱን መርሀ ግብር በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የአባይ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የወንደወሰን መንግሥቱ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደገለጹት የአባይ ቤዚን ፕላን ሲዘጋጅ ለሀገራችን አዲስ ሀሳብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ተግዳሮቶች እንደነበሩ ጠቅሰው ችግሮቹን ለመፍታት አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመር የቤዚን ፕላን ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት መቻሉን ገልፀዋል። ቤዚን ፕላኑን ለማዘጋጀት፤ በተፋሰሱ ውስጥ ያሉ አቅሞች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ የሁኔታ ዳሰሳ ሥራዎችን መሰራታቸውን ገልጸው፤ የአከባቢ ሁኔታ፣ የውሃ ሀብት አቅም፣ የተቋማዊና ህጋዊ ሁኔታና የአደጋ ስጋት ትንተናዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። የቤዚን ብላኑን ለመተግበር የተዘጋጁ ቴማቲክ ዕቅዶች ማለትም ዌትላንድ ማኔጅመንት፣ የመሬት መንሸራተት፣የውሃ ጥራት፣የቤዚን ኢንፎርሜሽን ማኔጅመንት፣የበለስና ዴዴሳ የውሃ ምደባ ዕቅዶች ቀርበው ውይይት ተደረጎባቸዋል፡፡